Fana: At a Speed of Life!

ለከተሞች ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እገዛ ወሳኝ ነው -ዶክተር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለከተሞች ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እገዛ ወሳኝ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በጎንደር ከተማ ከሃይማኖት አባቶችና ከሀገር ሽማግሌዎች ተወካዮች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ እየመከሩ ነው።

በጎንደር ከተማ ባለፈው ጊዜ የሀይማኖትን ሽፋን መሰረት አድርጎ የተፈጠረው ችግር ከዚህ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ እንዲቀለበስ በተደረገው ጥረት የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች እገዛ ከፍ ያለ ነበር ብለዋል።

በተመሳሳይ ከአሁን ቀደም ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም በተደረገው ጥረት የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የማይተካ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል ርዕስ መስተዳድሩ።

በክልሉ የሚገኙ ከተሞችን ሰላም አስተማማኝ በማድረግ ለተሻለ ዕድገት እንዲተጉ ለማድረግ የተለያዩ ተቋማት አደረጃጀቶች አበክረው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

በክብረወሰን ኑሩ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.