Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 7ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ “አዲስ አበባ የሰላምና የአብሮነት ከተማ” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ተካሄደ።

በክፍለ ከተማው መድሃኔአለም አደባባይ ላይ በተካሄደው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የከተማ አስተዳድሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

በዕለቱ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ጃንጥራር አባይ ፥ ስፖርት አይቋረጥምና የዘወትር ስራችን አድርገን ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር መትጋት ይኖርብናል ብለዋል።

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ሽታዬ መሃመድ በበኩላቸው ፥ ስፖርት ጤንነቱ የተጠበቀ ትውልድ ለማፍራት ወሳኝ ስለሆነ ሁላችንም ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ መነሳሳት አለብን ነው ያሉት።

በማህበረሰብ አቀፍ ስፖርት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ወረዳዎችም እውቅና መሰጠቱን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የቀጣይ ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ  አዘጋጅ  ልደታ ክፍለ ከተማ ከአዲስ ከተማ ዋንጫውን ተረክቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.