Fana: At a Speed of Life!

የጉምሩክ ኮሚሽን ከ14 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት እና ለአቅመ ደካሞች የሚውል የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን ከ14 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት እና ለአቅመ ደካሞች የሚውል የቁሳቁስ ድጋፍ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደረገ።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ 3 ሺህ 500 ኩንታል ሲሚንቶና 26 ሺህ 890 የቤት ክዳን ቆርቆሮዎችን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በመገኘት አስረክበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፥ ኮሚሽኑ ከህገ ወጦች እጅ የተያዙ የግንባታ ቁሳቁሶች ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ የአቅመ ደካሞችን ኑሮ ለማሻሻል እያደረገ ላለው ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

ሌሎች ተቋማትም የከተማዋን ዜጎች ኑሮ ለማሻሻል የበኩላቸውን ድጋፍ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘመኑ ደሳለኝ ÷ኮሚሽኑ በቅርቡ የ35 አቅመ ደካማ አባወራዎችን መኖሪያ ቤት ለማደስ የ15 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉንና ቤት የማደስ ሥራው መጀመሩን ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት ዋና ስራ አስፈጻሚው ሌሎች ተቋማትም የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ማለታቸውን የከንቲባ ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.