Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ በማዕድን እና ነዳጅ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ በማዕድን እና ነዳጅ ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና የኢኳቶሪያል ጊኒ የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትሩ ጋብሬል ምባጋ ኦቢአንግ ስምምነቱን ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ ሁለቱ ሀገራት በማዕድንና ነዳጅ ሃብታቸው አጠቃቀምና አሰራር ዙሪያ ያላቸውን ልምድ ለመጋራት የሚያስችል ነው ተብሏል።

ኢትዮጵያ የማዕድን ሃብት ባለቤት እንደመሆኗ እና የሃብት ካርታ ያላት በመሆኑ ይህንን ልምድ ለሃገሪቱ በማካፈል ረገድ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ነው የተባለው።

ኢኳቶሪያል ጊኒም በነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ዘርፍ ያላትን ልምድ ለኢትዮጵያ እንድታካፍል ያግዛታል።

ከዚህ ባለፈም የተደረሰው ስምምነት የአፍሪካ ሀገራት ሃብታቸውን በመጠቀም ያለውን ገበያ ለማሳደግ በጋራ የሚያደርጉትን ጥረት ለማሳካት ከፍ ያለ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
ሚኒስትሮቹ በዘርፉ በትብብር መስራት በሚችሉበት አግባብ ላይ መወያየታቸው ይታወሳል።

በሐይማኖት ኢያሱ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.