Fana: At a Speed of Life!

በክልሎች በተዘጋጁ ረቂቅ ሕጎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሎች በተዘጋጁ ረቂቅ ሕጎች ላይ ግብዓት ለማሰባሰብ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር እና የክልል ፍትህ ቢሮዎች ባዘጋጁት መድረክ በአራት ረቂቅ ሕጎች ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

ረቂቅ ሕጎቹ በክልሎች የሚዘጋጁ የጠበቆች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት እና የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ረቂቅ  ሕጎች መሆናቸው ተጠቁሟል።

ባለፉት ሶስት አመታት የተሰሩ የሕግ ማሻሻያዎች እና የነበሩ ተግዳሮቶችም በመድረኩ ተነስተዋል፡፡

የፀረ ሽብር ሕግ፣ የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አዋጅ፣ የሚዲያ ሕግ፣ የጠበቆች አስተዳደር፣ የሲቪል ማህበረስብ ድርጅቶች የአስተዳደር ስነ-ስርዓት፣ የጦር መሳሪያ የንግድ ህግ የተሻሻሉ ሕጎች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

ክልሎች ከፌደራል ሞዴል ሕጉ ጋር በማነጻጸር አካባቢያቸውን ታሳቢ በማድረግ አራቱ ህጎች ላይ ተወያይተው ያጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ውይይቱ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፥ በመድረኩ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አለምአንተ አግደውን ጨምሮ  የክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በፈትያ አብደላ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.