Fana: At a Speed of Life!

የታለመ የነዳጅ ድጎማ ሥርዓት በታቀደለት የጊዜ ማዕቀፍ ተግባራዊ ይደረጋል – ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የታለመ የነዳጅ ድጎማ ሥርዓት በታቀደለት የጊዜ ማዕቀፍ ተግባራዊ እንደሚደረግ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ አስታወቁ፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለትራንስፖርት ዘርፍ የክልልና ከተማ መስተዳደር ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በብሔራዊ ደረጃ ስለሚተገበረው የታለመ የነዳጅ ድጎማ ስርዓት ገለፃና ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

ሚኒስትሯ እንዳሉት፥ ነዳጅ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወትና ከህብረተሰቡ የኑሮ ሁኔታ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ መሆኑን ገልፀው፥ ሰፊ ጥናት ተደርጎ ለሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች የታለመ ድጎማ ለማድረግ መወሰኑን ነው ያስታወቁት፡፡

በሂደቱም እስካሁን ከነበረው ጥቅል የድጎማ ሥርዓት በመዘርጋት የሽግግር ጊዜ የሪፎርም ስራዎች በአግባቡ መከናወናቸውንና ለሪፎርሙ ተግባራዊነት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸውን ገልፀዋል፡፡

በዚህም የድጎማ ሥርዓቱ በታቀደለት የጊዜ ማዕቀፍ ተግባራዊ ይደረጋል ሲሉም መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በእስካሁኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በቂ መግባባት ላይ መደረሱን አስታውሰው፥ በአዲስ አበባ በፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎት፣ የከተማ ታክሲ አገልግሎት በሚሰጡ ተሽከርካዎች ላይ የብሔራዊ የታለመ የነዳጅ ድጎማ ስርዓት ማስተግበሪያን ተግባራዊ የስራ ሂደትን መመልከታቸውንና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ የለማው መተግበሪያ ስኬታማ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የክልልና ከተማ መስተዳደር ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተቀመጠው የትግበራ ሂደት የነበራቸውን ጉልህ ድርሻ ይበልጥ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.