Fana: At a Speed of Life!

ኤምባሲው የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ከኬንያ ፖሊስ ጋር ለመስራት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኬንያ የሚኖሩ ዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ከኬንያ ብሄራዊ የፖሊስ አገልግሎት ጋር በትብብር ለመስራት መስማማቱን አስታወቀ።

በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል የሚሲዮን መሪ አምባሳደር ሲራጅ ረሺድ ከኬንያ ብሄራዊ ፖሊስ አገልግሎት ዋና ኢንስፔክተር ጀኔራል ሂላሪ ሙትየምቢ ጋር በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን በተመለከተ ተወያይተዋል።

በውይይቱም አምባሳደር ሲራጅ በኬንያ የሚኖሩ ዜጎች ተገቢውን ክብር እንዲያገኙ እና በአንዳንድ የኬንያ ፖሊስ አባላት ለሚደርስባቸው እንግልት መፍትሔ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

የኬንያ ብሔራዊ ፖሊስ አገልግሎት ዋና ኢንስፔክተር ጄኔራል ሂላሪ ሙትየምቢ በበኩላቸው፥ በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መብት እንዲከበር ተቋሙ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል ብለዋል።

አያይዘውም የሚስተዋለውን ችግር ለመፍታት ቁርጠኛ መሆናቸውንና ለሚመለከታቸው የፖሊስ አካላት መመሪያ እንደሚያስተላልፉ ገልፀዋል።

በተጨማሪም ከጽህፈት ቤታቸው ለኤምባሲው አንድ ተጠሪ መመደባቸውንም አስረድተዋል።

ሁለቱ ወገኖች ህገወጥ ደላሎችን ለመከላከል በጋራ ለመስራት ከስምምነት መድረሳቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.