Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል ሕገ ወጥነትን ለመቆጣጠር እና ሕግን ለማስከበር የጸጥታ ኃይሎችን በየደረጃው ለማጠናከር ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 6፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት የጸጥታ ምክር ቤት በክልሉ እየተስፋፋ መጥቷል ያለውን “ሕገ ወጥነትን ለመቆጣጠር እና ሕግን ለማስከበር” በየደረጃው የጸጥታ ኃይሎችን ማጠናከር በሚያስችል ሁኔታ ላይ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የክልሉ የጸጥታ ምክር ቤት ዛሬ ባደረገው ስብስባ ነው “ሕገወጦች እና ሥርዓት አልበኞች” ያላቸውን አካላት መቆጣጠር እና የክልሉን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ግንባር ቀደም የትኩረት አቅጣጫ እንዲሆን ከውሳኔ ላይ መድረሱን ያስታወቀው።

የክልሉ የጸጥታ ምክር ቤት በስብሰባው የክልሉን የሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ በጥልቀት ገምግሟል።

እነዚህን ሕገ ወጥ ተግባራት በከተማም ሆነ በገጠር በአጭር ጊዜ ማረም ካልተቻለ የጋምቤላን ክልል ልማት የሚያስቀጠል እንደማይቻል የፀጥታ ምክር ቤቱ መግባባት ላይ ደርሷል።

በክልሉ ያለውን ሰላምና ልማት የሚያመክን፥ ሕገ ወጥነትንና የሥርዓት አልበኝነትን መናኸሪያ የሚያደርግ መሆኑን በመረዳት፥ ለሕዝብ ሰላምና ደህንነት ሲባል ችግሩን መልክ መያዝ እንደሚገባ የክልሉ የጸጥታ ምክር ቤት መወሰኑን ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.