Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ከጅቡቲ ዓለም አቀፍ ወደብ እና ነፃ ቀጠና ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከጅቡቲ ዓለም አቀፍ ወደብ እና ነፃ ቀጠና ሊቀመንበር አቡበከር ኦማር ሀዲ ጋር ተወያዩ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በጅቡቲ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ መሆኑን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ በጅቡቲ ቆይታቸው ከጅቡቲ ዓለም አቀፍ ወደብ እና ነፃ ቀጠና ሊቀመንበር አቡበከር ኦማር ሀዲ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የወጪ ንግድ እና የሎጂስቲክስ አገልግሎት የጋራ ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በውይይቱ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ መሳተፋቸውንም ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.