Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ከመንግስት የልማት ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር የእቅድ ውይይት እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከመንግስት የልማት ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር የእቅድ ውይይት እያደረገ ነው።

መድረኩን የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስጀምረውታል።

ውይይቱ መንግስት በልማት ዙሪያ ያለውን ፍላጎትና ቅድሚያ ሚሰጣቸው ጉዳዮች በተመለከተ እንዲሁም የመንግስት የልማት ድርጅቶች የሚያጋጥማቸውን ተግዳሮት ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ያወጣቸውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እቅድ ለማሳካት የልማት ድርጅቶች በትጋት መስራት እንዳለባቸው ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል።

እንደ ኦ ቢ ኤን ዘገባ በውይይቱ ማብቂያ የቀጣይ አቅጣጫ መመሪያዎች ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.