Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ኅብረት 110 ሺህ የዝንጀሮ ፈንጣጣ መከላከያ ክትባት ገዝቶ ለአባል ሀገራቱ ሊያከፋፍል ነው

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 110 ሺህ የዝንጀሮ ፈንጣጣ መከላከያ ክትባቶችን ገዝቶ ለአባል ሀገራቱ ሊያከፋፍል መሆኑን የአውሮፓ ኅብረት አስታወቀ ፡፡

የአውሮፓ ኅብረት ቀጣይነት ያለውን የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ለመከላከል 110 ሺህ መከላከያ ክትባቶችን ለመግዛት ከመድሃኒት አቅራቢዎች ጋር ዛሬ ስምምነት እንደሚፈርም ገልጿል፡፡

ኅብረቱ በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ ለአባል ሀገራቱ 110 ሺህ የዝንጀሮ ፈንጣጣ የመከላከያ ክትባቶችን ገዝቶ ማሰራጨት እንደሚጀምር የአውሮፓ የጤና እና የምግብ ደህንነት ኮሚሽነር ስቴላ ኪሪያኪደስ ተናግረዋል፡፡

የመከላከያ ክትባቱ ሰኔ ወር መጨረሻ ላይ መሰራጨት እንደሚጀመር እና የስርጭት ሂደትም ይበልጥ በበሽታው ለተጠቁ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ቅድሚያ በመስጠት እንደሚከናወን መናገራቸውን አናዶሉ ዘግቧል፡፡

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ የታየ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በ28 ሀገራት መከሰቱን የዓለም የጤና ድርጅት በቅርቡ ይፋ ባደረገው መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.