Fana: At a Speed of Life!

ሰላም ከሚፈልጉና እርቅ እናስቀጥላለን ከሚሉ ወገኖች ጋር ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት በክልሉ የተረጋጋ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ ሰላምን ከሚፈልጉ እና እርቅ እናስቀጥላለን ከሚሉ የክልሉ ወገኖች ጋር ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በካማሺ ዞን ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ላይ ከሃይማኖት አባቶችና ሀገር ሽማገሌዎች ጋር ተወያይተዋል።
ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በውይይቱ ላይ÷ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማገሌዎች በዞኑ ሰላም እንዲሰፍንና እርቀ ሰላም እንዲወርድ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
አክለውም÷ ከእርቀ ሰላሙ በኋላ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ፣ የተዘጉ መንገዶች ተከፍተው ዜጎች በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ፣ የተጎዱ የመንግስት ተቋማትና የግለሰብ ቤቶች በሕዝብ ተሳትፎ እንዲገነቡ እና ማህበረሰቡ ወደ መደበኛ የልማት ሥራው እንዲመለስ እቅድ ተይዞ እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጅ የተጀመረው ሥራ መሬት እንዳይነካ በታጣቂዎች በኩል በሥራ አፈፃፀም ወቅት በተፈጠረ ችግር በሚፍለገው ልክ ውጤት እንዳልተገኘም አብራርተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ አቶ ጌታሁን እንደገለጹት÷ መንግሥት ሰላም ከሚፈልጉና እርቅ እናስቀጥላለን ከሚሉ ወገኖች ጋር ለመሥራት ዝግጁ መሆኑ ነው፡፡
በመግባቢያ ሰነዱ ላይ ማድረግ የሚገባቸውን ጉዳይ በጋራ ተወያይተው በግልጽ እንዲያስቀምጡ ማሳሰባቸውን ከዞኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው÷ መንግስት በሆደ ሰፊነት ሁኔታወችን ተመልክቶ ሰላም ለመመለስ ያደረገው ጥረት አድንቀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.