Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ሰባተኛ የምገባ ማዕከል ለማቋቋም ስምምነት ተፈረመ

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር በአዲስ አበባ ሰባተኛ የምገባ ማዕከል ለማቋቋም የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሀና የሺንጉስ÷ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከዳሽን ባንክ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ሰባተኛ የምገባ ማዕከል ለማቋቋም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል፡፡

ሃላፊዋ የምገባ ማዕከሉን ለማቋቋም የሚውል የ40 ሚሊየን ብር የስምምነት ሰነድ ከተቋማቱ ጋር መፈረሙን አንስተዋል፡፡

በሚድሮክ ኢቨስትመንት ግሩፕ የኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አምባሳደር አሊ ሱሌማን በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ እያስተናገደች ያለው የተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች በተለይም በመዲናዋ የድጋፍ ፈላጊውን ቁጥሩ እንዲጨምር እንዳደረገው ተናግረዋል፡፡

ለዚህም ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከዚህ በፊት ተስፋ ብርሃን አሞዲ የተሰኘ የምገባ ማዕከል በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመተባበር አቋቁሞ እየሰራ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

አሁን ላይም ቁጥር ሁለት ተስፋ ብርሃን አሞዲ የምገባ ማእከል በልደታ ክፍለ ከተማ በማቋቋም የምገባ ስራው በማስፋት ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እንደወሰነ መግለጻቸውንም ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ተቋሙ ማዕከሉ በሚገነባበት የሚገኙ በዝቅተኛ ኑሮ ለሚኖሩ ስምንት አባወራዎች 8 የመኖሪያ ቤቶች ለመገንባት እንዲሁም ባሉበት የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ 16 የሱቅ ቤቶች በመገንባት ለማስረከብ እና በተረከበው የምገባ ማዕከል የሚገኘውን ቦታ በከተማ ግብርና ለማልማትና የልማቱ ውጤቱንም ለተመጋቢዎች እንዲያውል ኃላፊነት ወስዶ መፈራረሙን አንስተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.