Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሀገራችን ሀብቶች በኮንትሮባንድ ንግድ ድንበር ተሻግረው እንዳይወጡ መከላከል እንደሚገባ አስገነዘቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሀገራችንን ሀብቶች በኮንትሮባንድ ንግድ ድንበር ተሻግረው እንዳይወጡ መከላከል አስፈላጊ መሆኑን አስገነዘቡ፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ድንበር ተሻጋሪ የኮንትሮባንድ ንግድ ሀገራችን ከህጋዊ ንግድ የምታገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚያሳጣ ትልቅ ፈተና ሆኖ መቆየቱን አንስተዋል።
 
ከብቶቻችንን፣ ቡናችንንን፣ ወርቃችንን እና የሰብል ምርቶቻችንን በኮንትሮባንድ ድንበር ተሻግረው እንዳይወጡ መከላከላችንን አጠናክረን መቀጠል አለብን ሲሉም አሳስበዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.