Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር አወል ከባህሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ጋር ስለሰራተኞች ስምሪትና ደህንነት ጉዳይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 8፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህሬን የኢትዮጵያ ቆንስል ጄኔራል አምባሳደር አወል ወግሪስ መሀመድ ከባህሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ጋር ስለሰራተኞች ስምሪትና ደህንነት ጉዳይ ተወያዩ፡፡

አምባሳደሩ የሹመት ደብዳቤቸውን በባህሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር የቆንስላዎችና የአስተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ ተጠባባቂ ሃላፊ ለሆኑት ለአምባሳደር ኸሊል ያቆብ አል-ኻያት አቅርበዋል።

በዚህ ጊዜ ሁለቱ አምባሳደሮች በተለያዩ ሃገራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የተወያዩ ሲሆን÷ በተለይም የኢትዮጵያና የባህሬን ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸውም ስለሰራተኞች ስምሪትና ደህንነት ጉዳይ፣ በሁለቱ ሃገራት መካከል ተቋርጦ የነበረውን የአየር ትራንስፖርትን ስለማስቀጠል፣ በንግድና በቱሪዝም ዘርፍ ሁለቱን ሃገራት ለማስተሳሰር እንዲሁም የባህሬን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ስለሚሰማሩበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

ወደፊትም የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ይበልጠ በማጠናከር በቀጠናው ለሌላው ምሳሌ ሆኖ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅኅፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.