Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ወደ አውሮፓ የምትልከውን ጋዝ እየቀነሰች ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ወደ አውሮፓ የምታስገባውን የጋዝ አቅርቦቷን መቀነሷን እንደቀጠለች ነው፡፡

የሩሲያ ግዙፉ የጋዝ ኩባንያ ጋዝፕሮም በኖርድ ማስተላለፊያ መስመር- አንድ የተፈጥሮ ጋዝ ቧንቧ ላይ ሌላ ማስተላለፊያ መስመር እንደሚዘጋ አስታውቋል።

ይህም ወደ አውሮፓ የሚደርሰውን የጋዝ አቅርቦት በእጅጉ ይቀንሰዋል ነው የተባለው።

የጋዝ ተርባይን ሞተሮችን አምራች የሆነው የጀርመኑ ሲመንስ ኩባንያ የሚሰጠውን የጥገና አገልግሎት በጊዜው ማቅረብ አልቻለም በሚል ጋዝፕሮም ወቀሳ አቅርቧል።

ይህን ተከትሎም ሁለተኛውን ሞተር በፖርቶቫ መጭመቂያ ጣቢያ “በቴክኒክ ምክንያት” ለማቆም መወሰኑን ኩባንያው አስታውቋል።

በጣቢያው ያለው የምርት መጠንም ከዚህ ቀደም ከነበረበት 100 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር ወደ 67 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር ወርዷልም ነው ያለው።

ጋዝፕሮም እንዳለው ፥ በኖርድ ማስተላለፊያ መስመር- አንድ በኩል ያለው የጋዝ አቅርቦት መጠን በቀን ከ167 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር ወደ 100 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር ይቀንሳል ማለቱን የዘገበው ሺንዋ ነው።

በፈረንጆቹ 2011 የተጠናቀቀው አንደኛው የኖርድ ማስተላለፊያ መስመር በሰሜን ምዕራብ ሩሲያ የሚገኘውን ቪቦርግ ከተማን እና ጀርመንን በባልቲክ የባህር ዳርቻ በኩል ያገናኛል።

የመጀመሪያውን ማስተላለፊያ ለማገዝ ሁለተኛው የኖርድ ማስተላለፊያ መስመር በፈረንጆቹ 2021 ተጠናቋል ፤ ሆኖም ግን ሩሲያ በየካቲት ወር ከዩክሬን ጋር ጦርነት ውስጥ ከገባች በኋላ ተቋርጧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.