Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የሠራተኞች የኑሮ ውድነት ጫናን ለማቃለል የተለያዩ አማራጮች ይተገበራሉ – አቶ ጃንጥራር ዓባይ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሠራተኞች የኑሮ ውድነት ጫናን ለማቃለል የተለያዩ አማራጮችን እንደሚተገብር አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በአዲስ አበባ በከተማ ማዕከላት ለሚገኙ ዳይሬክተሮችና የቡድን መሪዎች ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የስራ ፈጠራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር÷ አስተዳደሩ የተለያዩ የቤት ልማት ፕሮግራሞችን በመቅረጽ የአስተዳደሩን ሠራተኞች የቤት ችግር ለማቃለል የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ መቆታቸውን አንስተዋል፡፡
በቀጣይም የቤት ልማት ሥራዎችን በማስፋት ሠራተኛውን ተጠቃሚ ለማድረግ ጥረት ይደረጋል ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በመንግስት መዋቅር ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራተኛ መኖሩን ገልጸው÷ ለዚህ ኃይል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች መስጠት የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ ለማስቀጠል ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ ሉሌ በሦስት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልጸው÷ ስልጠናው ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.