Fana: At a Speed of Life!

ጅማ ከተማን ጨምሮ በጅማ እና ቡኖ በደሌ ዞኖች ለሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የኮምፒውተር ድጋፍ ተደረገላቸው

አዲ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ እና ካማራ ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ በጅማ ከተማ፣ በጅማ ዞን እና ቡኖ በደሌ ዞን ለሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 500 ኮፒምፒውተሮችን በድጋፍ መልክ አበረከቱ፡፡
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባፊጣ በርክክብ መርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የጅማ ዩኒቨርሲቲ በአካባቢው የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት አሰጣጥ ለማዘመን እና በቴክኖሎጂው የተደገፉ እንዲሆኑ ለማድረግ ከካማራ ኢዱኬሽን ጋር በመተባበር ድጋፉን አድርጓል ብለዋል፡፡
ኮምፒውተሮቹ ለሁሉም የትምህርት አይነቶች አጋዥ መጻሕፍት ክምችት እንዳለባቸው እና ለመምህራንም አጋዥ መጻሕፍት እንዳካተቱ ተገልጿል።
በተጨማሪም ኢንተርኔት አገልግሎት በሌለበት መጠቀም የሚያስችሉ የዊኪፒዲያ አገልግሎት፣ ለአይነስውራን ማንበቢያ ሶፍትዌር እንዲሁም ለመማር ማስተማር አጋዥ የሆኑ የተለያዩ አጋዥ ሶፍትዌሮች የተጫኑባቸው መሆኑም ተመላክቷል፡፡
በአጠቃላይ ለኮምፒውተሮቹ ግዢ 20 ሚሊየን ብር እንደወጣበት ዶክተር ጀማል ጠቁመው÷ ድጋፍ የተደረገላቸው ትምህርት ቤቶች ኮምፒውተሮችን ለመማር ማስተማሩ ስራ አጋዥ አድርገው በአግባቡ እንዲጠቀሙባቸው ጠይቀዋል፡፡
በወርቃአፈራሁ ያለው
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.