Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በብሪክስ ጉባዔ ላይ እንድትሳተፍ ከቻይና ግብዣ ቀረበላት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ በምታስተናግደው የብሪክስ ጉባዔ ኢትዮጵያ እንድትሳተፍ ግብዣ አቀረበች፡፡

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጉባዔው ላይ እንዲሳተፉ መጋበዛቸውን ያስታወቁት በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩአን መሆናቸውም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ተመላክቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተሥፋዬ ይልማ በኢትዮጵያ የቻይና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርን ዣኦ ዢዩአን ጋር የሀገራቱን የቀደመ ወዳጅነት እንዲሁም የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋልም ነው የተባለው፡፡

የብሪክስ አባል ሀገራት የሚባሉት – ብራዚል ፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ ሲሆኑ ሀገራቱ በጥምረት እስከ ፈረንጆቹ 2050 ዓለምአቀፉን የኢኮኖሚ መሪነት ለመቆጣጠር አቅደው ይሠራሉ፡፡

በብሪክስ አባል ሀገራት ጉባዔ ÷ ዓላማውቸውን ለማሳካት በዘላቂ የልማት ግቦቻቸው አፈጻጸም እና የሀገራቱን ፖለቲካዊ ሁኔታዎች እንዲሁም ወቅታዊ ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ይመለከታሉ።

በዚህ ዓመቱ ጉባዔ ላይ ከ10 በላይ ታዳጊ ሀገራት እንዲሳተፉ ግብዣ ቀርቦላቸዋል ።

በሌላ በኩል አምባሳደር ተሥፋዬ ይልማ ÷ ቻይና በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና ዕድሎች በመሳተፍ እያደረገች ያለዉን ጥረት ኢትዮጵያ እንደምታደንቅም መናገራቸው ተመልክቷል።

በወይይቱ በቻይና እና በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ ከቀናት በኃላ በሚካሄደው የአፍሪካ ቀንድ የሠላም ጉባዔ ዝግጅት አፈፃፀም እና በቻይና አፍሪካ የትብብር ማዕቀፍ ላይ መምከራቸው ነው የተጠቆመው።

የቻይናዉ አምባሳደር የቻይና-አፍሪካ የትብብር ማዕቀፍ ዉጤቶችን ለመገምገምም በቻይና በነሃሴ ወር ላይ ለሚካሄደው የምክክር መድረክ ኢትዮጵያ እንድትሳተፍም ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.