Fana: At a Speed of Life!

አዲስ ወግ – ዐብይ ጉዳይ ሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ‘የጽንፈኝነት መገለጫዎችና ውጤቶቹ’ በሚል ርዕስ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው አዲስ ወግ – ዐብይ ጉዳይ ሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ‘የጽንፈኝነት መገለጫዎችና ውጤቶቹ’ በተሰኘ ርዕስ ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ የስነ አዕምሮ ሀኪም የሆኑት ዶክተር ምሕረት ደበበ፣ ከሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ጄይላን ወልይ ፣ ዶክተር ሰለሞን ተሾመ በሀሳብ አቅራቢነት የተሳተፉበት ሲሆን ፥ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና አዘጋጅ አመት አሕመድ ክፍለ ጊዜውን አመቻችተዋል።

በዚህ ወቅት ዶክተር ምህረት እንዳሉት ፥ “መሐል ለሥራ ሲሆን መልካም አይደለም ፤ ሥራ መካከለኛ ከሆነ ጥሩ አይደለም፤ ልህቀት ላይ መድረስ አለበት፤ ጽንፈኝነት ግን ልህቀት የለውም፤ ወደ መሐል ወደ አማካይ መምጣት ያስፈልጋል”፡፡

አክለውም ፥ ጽንፈኝነት ከልዩነት ብቻ ሳይሆን ከእኩልነት ይልቅ የበላይ ከመሆን ፍላጎትም እንደሚመነጭ ጠቅሰው፥ ጽንፈኝነት ከበታችነትና የጎደለብኝ አለ ከሚል ስሜት ስለሚነሳ እኩልነትን ማስፈን እንዲጠፋ ያግዛልም ነው ያሉት፡፡

ፕሮፌሰር ጄይላን ወልይ በበኩላቸው ፥ “ጽንፈኝነት ውስጠ ስሪቱ ፖለቲካዊ ነው ፤ በእሳቤ የሚያራምደው ዓላማ አለው ፤ በባህሪያዊ አወቃቀሩም ውድመት አለበት” ይላሉ።

ጽንፈኝነት ከምክንያታዊ ፖለቲካ ወደ ስሜት መራሽ ፖለቲካ እንደሚያደርስ ገልጸው ፥ በማንነት/በታሪክ ዙሪያ የብሔር ጽንፈኝነት አራማጆች መድኅነ ስብስብ ላይ ያተኮረ የብሶት፣ የስጋት፣ የተስፋ (ካወደማችሁ በኋላ ለእናንተ መልካም ነገር ይገኛል) የሚል ፖለቲካን ያራምዳሉ ሲሉ ሃሳባቸውን ገልጸዋል።

ዶክተር ሰለሞን ተሾመ በርዕሰ ጉዳዩ በሰጡት ሃሳብ ፥ ሀይማኖታዊ ጽንፈኝነት እንደ መገፋት፣ መገለል የመሳሰሉ ውስጣዊ መንስዔዎች እንዳሉት አንስተዋል።

አያይዘውም ውጫዊ መንስዔዎቹ ደግሞ የገንዘብ፣ የሞራል፣ የፖለቲካ፣ የመሳሰለውን ድጋፍ ማግኘት ናቸው መሆናቸውን በመጥቀስ፥ ዐውዳዊ መንስዔዎቹ ደግሞ ጠንካራ ያልሆነ ስርዓተ መንግሥት፣ የሕግ የበላይነትና ሙስና እንደሆኑ አውስተዋል።

የሀይማኖት ጽንፈኝነትን ለመከላከል ከየሀይማኖቱ ጋር ተዛምዶ እንደ ሌለው በመገንዘብ፣ የሀይማኖት ተቋማት በጋራ መሥራት አለባቸው ፥ ይህን እንዲከውኑም ድጋፍ መስጠት ያሻል ብለዋል።’

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.