Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ እየተካፈለች ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ እየተካፈለች ነው።

ምክር ቤቱ ለአንድ ወር የሚያካሂደውን 43ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት፣ በይነ መንግስታዊ ድርጅቶች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በመካፈል ላይ ይገኛሉ።

በስብሰባው ”ጥሪ ለተግባር” በሚል ርዕስ ሰባት መሰረታዊ ግቦችን ያቀፈ ዕቅድ ይፋ ተደርጓል።

በመክፈቻው ላይ የተመድ የ74ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ፕሬዚዳንት፣ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ እንዲሁም የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነርን ጨምሮ ከ90 በላይ ሃገራት በከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ደረጃ ንግግር አሰምተዋል።

ኢትዮጵያን በመወከል በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ባንተይሁን ጌታሁን የተመራና ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና በጄኔቫ የኢፌዴሪ ቋሚ መልዕክተኛ ፅህፈት ቤት የስራ ኃላፊዎችን ያቀፈ የልዑካን ቡድን ታሳታፊ ነው።

የልዑካን ቡድኑ በተለይም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሁሉን አቀፍ ለውጥ ተከትሎ የተመዘገቡ እመርታዎችን በማስተዋወቅ ተጨማሪ ድጋፍ ማግኘት በሚቻልበት አግባብ ላይ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.