Fana: At a Speed of Life!

የጀርመን መንግስት ለኢትዮጵያ ከ500 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአ ይ ሲ ቲ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመን መንግስት ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከ500 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአ ይ ሲ ቲ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
ድጋፍ ከጀርመን መንግስት የኢኮኖሚና ትብብርና ልማት ባንክ የተገኘ ሲሆን÷ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የአይ ሲ ቲ መሰረተ-ልማት ማስፋፊያ የሚውል ነው ተብሏል፡፡
 
የአይ ሲ ቲ መሰረተ-ልማት ማስፋፊያው በተመረጡ 20 የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ተግባራዊ እንደሚደረግም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የሶፍትና የሀርድ ዌር ልማት እንዲሁም የቀጥታ የበይነ መረብ ሥልጠናን ጨምሮ በዘርፉ ለሚተገበረው የዲጂታላይዜሽን ሥራ የላቀ ፋይዳ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡
 
ከ500 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት ወደ አገር ውስጥ የገባውን ድጋፍም የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክ ዶክተር በከር ሻሌ እና የቴክኒክንና ሙያ ኢንስቲቲዩት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.