Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የወላይታ ሶዶ ከተማ አውሮፕላን ማረፊያ እና የዳቦና ዱቄት ፋብሪካን የግንባታ ሂደት ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የወላይታ ሶዶ ከተማ አውሮፕላን ማረፊያ እና የዳቦና የዱቄት ፋብሪካ የግንባታ ሂደት ጎበኙ፡፡

በጉብኝት መርሐ ግብሩ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ፣የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ ፣ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሥራ ጉብኝት በደቡብ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ በዛሬው ዕለት ገብተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና በእርሳቸው የተመራው ልዑክ የወላይታ ሶዶ ከተማ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን እና በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት እየተካሄደ ያለውን የዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ የግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል።

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በመለሰ ታደለ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.