Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ሂላላ የነዳጅ እና ተፈጥሮ ጋዝ ማውጫ ፕሮጀክት ተጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ዑማ እና የግብርና ሚኒስትሩ ዑመር ሁሴን ከቱርክ ባለሃብቶች ጋር በመሆን በሶማሌ ክልል ሂላላ የነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ማውጫ ፕሮጀክትን ጎበኙ፡፡

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ዑማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀማችን የእድገት ተስፋችንን ይወስናል ብለዋል።

የተፈጥሮ ጋዝ ከተስፋዎቻችን አንዱ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ይህን ሃብታችንን ለማልማት የመንግስትንም ይሁን የግል ክፍለ ኢኮኖሚውን በማሳተፍ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንድትሆን እናደርጋለን ብለዋል።

በዛሬው ዕለትም ከግብርና ሚኒስትሩ ዑመር ሁሴን እና የተፈጥሮ ጋዝን በመጠቀም ማዳበሪያን ለማምረት ከሚፈልጉ የቱርኩ ካሊክ ሆልዲንግ ባለሃብቶች ጋር በመሆን በሶማሌ ክልል ሂላላ የነዳጅ እና ተፈጥሮ ጋዝ ማውጫ ፕሮጀክት ሳይትን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም ኩባንያው በዘርፉ ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት ያለው መሆኑን ያነሱ ሲሆን ፥ በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገባ ተገቢው ድጋፍ እንደሚደረግለትም ነው የጠቀሱት።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.