Fana: At a Speed of Life!

ጤና ሚኒስቴር “ማስተርካርድ ዌልነስ ፓስ” የተሰኘ የጤና መረጃ አያያዝ መተግበሪያ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤና ሚኒስቴር “ማስተርካርድ ዌልነስ ፓስ” የተሰኘ ዲጂታላይዝድ የጤና መረጃ አያያዝ መተግበሪያ ይፋ አደረገ፡፡
 
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷የዲጂታላይዝድ ጤና መረጃ አያያዝ መተግበሪያ በጤናው ዘርፍ የሚስተዋለውን የመረጃ አያያዝ ችግር እንደሚቀርፍ ገልጸዋል፡፡
 
መተግበሪያውን ወደ ስራ ለማስገባት ከማስተር ካርድ፣ ጂ ኤ ቪ አይ እና ጄ ኤስ አይ ከተሰኙ ተቋማት ጋር ስምምነት መፈረሙንም ነው ሚኒስትሯ የገለጹት፡፡
 
“ማስተርካርድ ዌልነስ ፓስ” የተሰኘው ይህ መተግበሪያ÷ ለ15 ወራት የሚቆይ የሙከራ ምዕራፍ በመላ አገሪቱ በተመረጡ የጤና ተቋማት ላይ የሚተገበር እንደሆነ ተመላክቷል፡፡
 
መተግበሪያው ያለ ኢንተርኔት አገልግሎት የጤና መረጃዎችን መመልከት እንደሚያስችልም ነው የተጠቆመው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.