Fana: At a Speed of Life!

አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የአርባምንጭ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የአርባምንጭ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታን ሂደትን ጎብኝተዋል፡፡
ዋና አፈ ጉባኤው በጉብኝታቸው ወቅት ÷ በእውቀትና ስነምግባር የታነፀ ሀገር ተረካቢ ዜጋ ለማፍራት የዞኑ አስተዳደር የአዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ በመጀመሩን አመስግነዋል።
የትምህርት ቤቱ ግንባታ ተጠናቆ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲጀምር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በበኩላቸው የአርባምንጭ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ አፈፃፀም 40 በመቶ መድረሱን ገልጸው÷ ግንባታው በታቀደለት ጊዜ ተጠናቆ በ2015 የትምህርት ዘመን ለመማር ማስተማር ስራ እንዲውል በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
አዳሪ ትምህርት ቤቱ ከ400 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ እንደሚገኝ የጋሞ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.