Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው በታክስ ምክንያት የተወረሱ አልባሳትን ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር 5 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው ታክስ ባለመክፈላቸው ምክንያት የተወረሱ አልባሳትን ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረክቧል።

ሚኒስቴርሩ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ በሴቶች ለተመሰረቱ አራት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ነው ስጦታውን ያበረከተው።

የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ተገቢውን የመንግስትና የህዝብ ጥቅም ሰውረው የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን በሚፈፀሙ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።

መሰል የኮንትሮባንድ ስራዎች በጉምሩክ ጣቢያዎችና ኬላዎች ቁጥጥር ብቻ የሚገቱ አለመሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ፥ ህብረተሰቡ ድርጊቱ የሃገርን ደህንነትና ኢኮኖሚ አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር መሆኑን በመገንዘብ ትብብሩን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር በተከናወነ ስራ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ምርቶች መያዛቸው ተመላክቷል።

በሶዶ ለማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.