Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር ኢትዮጵያ በሕብረቱ በሚደረገዉ ለውጥና ማሻሻያ እገዛ እንድታደርግ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር ዶ/ር ሞኒክ ንሳንዛባጋንዋ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው ምክትል ሊቀ-መንበር ሞኒክ ኢትዮጵያ በሕብረቱ በሚደረገው ለውጥ እና ማሻሻያ እገዛ እንድታደርግ ጠይቀዋል ።

አምባሳደር ተስፋዬ የአፍሪካ ሕብረት መዋቅር የተበታተነ በመሆኑ ስራዎችን በጋራ ለመምራት፣ የተሟላ አመራር እንዲሰጥ ለማድረግ የመዋቅር ማሻሻያው ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል ።

ለዚህም የባለሙያዎች ቅጥር፣ ስምሪት ፍትሃዊ እና አሳታፊ በሆነ መንገድ እንዲፈጸም ኢትዮጵያ እንደ አስተናጋጅ ሀገር ለአዲሱ ለውጥ ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል ።

የፋይናንስ መዋቅር ለዉጥ ፣ የሰዉ ሀይል መረጣ እና ምልመላ በብቃት እና በክህሎት እንዲሁም በትምህርት ዝግጅት መለኪያ በሕብረቱ የስራ ክፍሎች አጠቃላይ ስምሪት እንደሚሰጥም በውይይቱ ተገልጿል ።

ምክትል ሊቀ-መንበር ሞኒክ÷በሕብረቱ መዋቅራዊ ለዉጥ ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች በጋራ እየተመካከሩ እንዲፈፀም ኢትዮጵያ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ያላቸውን ተስፋ መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.