Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የማዕድን ሃብትን በዘላቂነት ለማልማት ያለመ የማዕድን ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኝ የማዕድን ሃብትን በዘላቂነት ለማልማት ያለመ የመጀመሪያው ክልል አቀፍ የማዕድን ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው።

“የማዕድን ሀብት ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ የሚገኘው ሲምፖዚየም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል አመራሮች፣ ተመራማሪዎች፣ በዘርፉ የተሠማሩ ባለሃብቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በመድረኩ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፥ በተለይም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ክልሉ የማዕድን ሀብቶችን ከማስተዳደር ባለፈ የክልሉ ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው ማለታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሲምፖዚየሙ የክልሉን ማዕድን ሃብትን በዘላቂነት ለማልማት የሚያስችሉ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት የሚደረግ ሲሆን÷ በዘረፉ ልማት ላይ ለሚስተዋሉ ችግሮች የመፍትሄ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ክልሉ እምነበረድና ወርቅን ጨምሮ የተለያዩ የማእድን ሀብቶች ባለቤት ነው።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.