Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ነገ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በነገው ዕለት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11፡ከ30 እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ለተሸከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በመስቀል አደባባይ ባዘጋጀው ስፖርታዊ ዝግጅት እና መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ በሚያደርገው የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ምክንያት ነገ ሰኔ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ከንጋቱ 11፡ከ30 እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች ከዚህ በታች የተገለፁት መንገዶች ዝግ መሆናቸውን ተገንዝበው ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ ነው ፖሊስ ያሳሰበው፡፡
በዚህም መሰረት
– ከወሎ ሰፈር መገንጠያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አካባቢ
– ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን በሰዓት 50 እና 80 ኪሎ ሜትር በተፈቀደባቸው በሁለቱም አቅጣጫ
– ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቴአትር የሚወስደው የቀድሞ ደሳለኝ ሆቴል።
-ከንግድ ማተሚያ ቤት በኦርማ ጋራዥ በፍል ውሃ ወደ መስቀል አደባባይ ኦርማ ጋራዥ መስቀለኛው ላይ
ከ4 ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ ኮንሰን ወይም ወደ ሸራተን ሆቴል የሚወስደው መንገድ ላይ፡፡
-ከሳር ቤት አካባቢ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች አፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት፡፡
– ከፒያሳ አካባቢ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ፖስታ ቤት ትራፊክ መብራት ላይ
– ከካዛንቺስ በፍል ውሃ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ እና በተመሳሳይ ካዛንቺስ የትራፊክ መብራት በባምቢስ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ የትራፊክ መብራት ላይ፡፡
– ከጎፋ በቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ለገሐር አዲሱ መንገድ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛው ላይ
-ከቄራ ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ጠማማ ፎቅ አካባቢ፡፡
– ከጦር ኃይሎች ፣ በልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወሰደው መንገድ ባልቻ ሆስፒታል መስቀለኛ፡፡
-ከመርካቶ በበርበሬ በረንዳ ወደ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው አረቄ ፋብሪካ አካባቢ
– ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች አጎና ሲኒማ አካባቢ
-ከጎተራ በመሿለኪያ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ መንገዱ የሚዘጋ ሲሆን÷ ህብረተሰቡ ከፖሊስ የተሰጠውን መረጃ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ፖሊስ ጠይቋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.