Fana: At a Speed of Life!

ከሩሲያ ጋር መነጋገር “እጅግ አስፈላጊ” መሆኑን የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 11፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሩሲያ ጋር መነጋጋር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ ተናገሩ፡፡
ለዲ ፒ ኤ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ከበርካታ የአውሮፓ ሀገራት ትችት ቢደርስባቸውም ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ግንኙነት መፍጠርና መነጋገር አስፈላጊ ነው።
ኦላፍ ሹልዝ ከፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በመሆን እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጎን ለጎን ከፑቲን ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለመቀጠል መወሰናቸውን አስረድተዋል፡፡
ከሩሲያ ጋር መነጋገር በጣም አስፋላጊ ነው ያሉት ሹልዝ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እንዳደረጉት እኔም ከፑቲን ጋር መነጋገሬን እቀጥላለሁ ብለዋል፡፡
አቋማቸውን ግልፅ ለማድረግ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን እንደሚጠቀሙ በመግለፅ በተለይም አውሮፓውያን ለዩክሬን ሰላም መስፈን እንዳማይጥሩ እና ኬቭ ግጭቱን ለማስቆም ስምምነት ማድረግ እንዳለባት ለፕሬዚዳንት ፑቲን መናገር እንደሚፈልጉም ነው የተናገሩት።
ሞስኮም ወታደሮቿን ከዩክሬን ግዛት እንድታስወጣ እና በኪዬቭ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ስምምነት ላይ እንድትደርስም ኦላፍ ሹልዝ ጠይቀዋል።
ከቀናት በፊት ኦላፍ ሹልዝን ጨምሮ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ እንዲሁም የሮማኒያው ፕሬዝዳንት ክላውስ ሎሃኒስ በኬቭ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።
በጉብኝቱ ወቅት ሹልዝ ጦርነቱ በፍጥነት እንዲቆም የጠየቁ ሲሆን የዩክሬንን የአውሮፓ ህብረት አባልነት በመደገፍ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪን በሚቀጥለው የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉ መጋበዛቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.