Fana: At a Speed of Life!

በተያዘው አመት በኢትዮጵያ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ቶን የስንዴ ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል – ብሉምበርግ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዚህ አመት በኢትዮጵያ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ቶን የስንዴ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ግብርና ሚኒስቴርን ጠቅሶ ብሉምበርግ ዘገበ።
ብሉምበርግ በዘገባው ዘንድሮ ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀው የስንዴ ምርት ካለፈው አመት አንጻር የ70 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑንም አመላክቷል።
ባለፈው አመት 1 ነጥብ 42 ሚሊየን ቶን የስንዴ ምርት መገኘቱን ዘገባው አስታውሷል።
ይህም ሀገሪቱ በፈረንጆቹ 2023 የስንዴ ምርትን ለውጭ ገበያ ለመላክ የያዘችውን ዕቅድ ለማሳካት ያግዛል ተብሎ እንደሚጠበቅም በዘገባው ጠቅሷል።
ኢትዮጵያ የስንዴ ፍጆታዋን ከውጭ በማስገባት የምትሸፍን ሲሆን፥ ከአዝዕርት ፍጆታዋ ውስጥ 27 በመቶውን ከዩክሬን 15 በመቶውን ደግሞ ከሩሲያ ታስገባለች።
በፈረንጆቹ 2023 ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በሃገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን ታቅዶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን፥ ለዚህም በክላስተር የስንዴ ማሳ እየለማ ይገኛል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.