
እንደ ቅድመ አያቶቻችን ማንኛውንም ዓይነት ፈተና በድል የምንወጣ ጠንካራ ህዝቦች ነን – ፕሬዚዳንት ፑቲን
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያውፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን የምዕራቡ ዓለም የኢኮኖሚ ማዕቀብ አይሰብረንም ፤ እንዲያውም ይበልጥ ያጠነክረናል ሲሉ ገለጹ፡፡
ቭላድሜር ፑቲን ÷ እንደ ቅድመ አያቶቻችን ማንኛውንም ዓይነት ፈተና የመጋፈጥ ብቃት እንዳለን ያለፉት ዘመናት የሩሲያ ታሪክ ማሳያ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ፑቲን ÷ የሩሲያ ኢንተርፕራይዞች የሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንታቸውን እንዲያሳድጉ እና የሀገራቸውን “ግዙፍ አቅም” ተረድተው ምዕራባውያን በኢኮኖሚ ሀገረ-ሩሲያን ለማጥፋት የሚያደርጉትን ጥረት መና እንዲያስቀሩ ማሳሰባቸውን ሲጂቲ ኤን ዘግቧል።