Fana: At a Speed of Life!

የኮንትሮባንድ ንግድ እየፈጠረ ያለውን የፀጥታ ችግር ለመከላከል የተቋማት የተቀናጀ ስራ ሊጠናከር ይገባል – አቶ ሙስጠፌ መሀመድ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮንትሮባንድ ንግድ እየፈጠረ ላለው የጸጥታ ችግር የፌደራልና የክልሎች የፍትህና ፀጥታ ዘርፍ ተቋማት የተቀናጀ መከላከል ስራዎች ሊጠናከሩ እንደሚገባ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ አስታወቁ፡፡

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የተዘጋጀ የፀረ ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ መከላከል የንቅናቄ መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ዛሬ ተጀምሯል።

በመድረኩ የተገኙት የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፥ ህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ በአገር ኢኮኖሚ ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባሻገር በማህበራዊና በፀጥታ ማስከበር ስራዎች ላይ ትልቅ መሰናክል በመሆኑ የፌደራልና የክልሎች የፍትህና ፀጥታ ዘርፍ ተቋማቶች ካለፉ ዓመታት በበለጠ የተቀናጀ መከላከል ስራዎች ሊከውኑ ይገባል፡፡

የምሥራቁ የኢትዮጵያ ክፍል የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ እንቅስቃሴውን ለመግታት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች በተለይም ከለውጡ ወዲህ መሻሻሎች እየታየበት ቢሆንም ፤ በሚፈለገው መጠን መግታት ባለመቻሉ ከማስተማር ጎንለ ጎን የተጠናከረ የህግ ማስከበር ስራዎች በንቅናቄ ደረጃዎች መከወን እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ፣ የጉምሩክ ኮምሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቀበታ እና የፍትህና ፀጥታ ዘርፍ አመራሮችና ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል፡፡

በንቅናቄ መድረኩ በቀጣይ በአገር አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ የፀረ ኮንትሮባንድ መከላከል ስራን ለመከወን የሚያስችል አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ይጠበቃል፡፡

በጎህ ንጉሱ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.