Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ቡድን ሽንፈትና ኪሳራ እየደረሰበት በመሆኑ የቀቢፀ ተስፋ እርምጃዎችን በአፀፋው እየወሰደ ይገኛል – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፀጥታ አስከባሪ አካላትና በህዝቡ የተባበረ እርምጃ በአሸባሪውና ፅንፈኛው ቡድን ላይ በደረሰበት ሽንፈትና ኪሳራ የቀቢፀ ተስፋ እርምጃዎችን በአፀፋው እየወሰደ ይገኛል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡

 

አቶ ደመቀ ጉዳዩን አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ በቅርብ ጊዜ በጋምቤላ አካባቢ ያደረገው ሙከራ ሲከሽፍበት በምዕራብ ወለጋ በጊምቢ አካባቢ ደግሞ በንፁሃን ዜጎች ላይ በተለይም በህጻናትና በሴቶች ላይ ያካሄደው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ እና ኢሰብዓዊ ነው ብለዋል፡፡

 

አቶ ደመቀ በተለያዩ አካባቢዎች ቡድኑ በወሰደው እኩይ የጥፋት እርምጃ ምክንያት በንፁሃን ወገኖቻችን ላይ ለደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል፡፡

 

በመንግስት በኩል ህግ የማስከበር እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ላረጋግጥ እወዳለሁ ብለዋል አቶ ደመቀ በጽሑፋቸው።

 

በቀጣይ ተጎጂ ቤተሰቦችን የማረጋጋት፣ የመደገፍ እና መልሶ የማቋቋም ስራ በትኩረት እንደሚሰራ እና አሸባሪዎችን እና ጽንፈኞችን ለህግ የማቅረቡ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.