Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል የአረንጎዴ አሻራ መርሃ- ግብር አየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በአፋር ክልል የአረንጎዴ አሻራ መርሃ- ግብር አየተካሄደ ነው::

በመርሃ-ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳፉ ይገኛሉ::

በክልል ደረጃ 14 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል እቅድ የተያዘ ሲሆን ÷የዛሬው መርሃ ግብርም የዚሁ እቅድ አካል መሆኑም ታውቋል::

በዚህ ክረምት ከ4ሚሊየን በላይ ችግኝ ሲተከል ቀሪው 10ሚሊየን ደግሞ ከመስከረም በኋላ በክልሉ ለችግኝ ተከላዉ ተስማሚ በሆነ የአየር ንብረት ወቅት እንደሚተከል ተመልክቷል ::

የችግኝ ተከላው በሁሉም የክልሉ አስተዳደር እርከኖች አየተከናወነ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዛሬው ቀንም ከ1ሚሊየን በላይ ችግኝ እንደሚተከል ይጠበቃል::

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.