Fana: At a Speed of Life!

ለ4ኛው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከተዘጋጁት ችግኞች መካከል 52 በመቶዎቹ የምግብ ዋስትና የማረጋገጥ ጥረትን የሚያግዙ ናቸው – ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው ዓመት ከተዘጋጁት 7 ነጥብ 6 ቢሊየን ችግኞች መካከል 52 በመቶ የሚሆኑት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚያግዙ መሆናቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
አራተኛው ዙር የ2014 የአረንጓዴ ዐሻራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ በጉለሌ የእጽዋት ማዕከል ተካሂዷል፡፡
በዘንድሮው ዓመት ስድስት ቢሊየን ችግኝ ለመትከል መታቀዱን የጠቆሙት አቶ ዑመር÷ ነገር ግን 7 ነጥብ 6 ቢሊየን ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡
ባለፉት ሦስት ዓመታት 18 ቢሊየን ችግኞች መተከላቸውን ገልፀው፥ ከ80 በመቶ በላይ ያህሉ መጽደቃቸውንም አስረድተዋል፡፡
ችግኞቹ የመሬት መራቆትን በመግታት፣ የአየር ንብረት ለውጥን በመቀነስ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና አላቸው ።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.