Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ኅብረት በሩሲያ የምግብ እና የማዳበሪያ አቅርቦቶች ግዢ ላይ ማዕቀብ አለመጣሉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሩሲያ ምግብ እና ማዳበሪያ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም አካል ማዕቀብ ሳይፈራ ግዢ መፈጸም እንደሚችል የአውሮፓ ኅብረት የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል አስታወቁ፡፡

ቦሬል ይህን ያሉት የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል በዘለቀው ወታደራዊ ግጭት ምክንያት ጥቁር ባህር ወደቦች ላይ የተያዘውን የዩክሬን ወጪ የእህል ንግድ ማስለቀቅ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

እንደ ዓለም ንግድ ድርጅት መረጃ ከ22 እስከ 25 ሚሊየን ቶን እህል በዩክሬን ወደቦች ተይዟል፡፡

ምዕራባውያን የዩክሬንን የእህል ወጪ ንግድ ሩሲያ አግዳለች በሚል በተደጋጋሚ ውንጀላ አቅርበዋል።

ሩሲያ ደግሞ እህሉ በነጻ ንግድ በጥቁር ባህር ወደቦች በኩል ለዓለም እንዲደርስ እፈልጋለሁ፤ ነገር ግን ዩክሬን በባህሩ ላይ ካላት ልዩ ፍላጎት የተነሳ ወታደራዊ ኃይሏ ወደቦቹን በመቆጣጠሩ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል ማለቷን አር ቲ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ከአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባም የአውሮፓ ሀገራት ተጨባጭ ውጤት እየጠበቁ ይገኛል ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.