Fana: At a Speed of Life!

ለምርት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ከገበያ ላይ ማግኘት አዳጋች ሆኖብኛል -የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማኅበር

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማኅበር ለምርት የሚያስፈልጉኝን ግብዓቶች ከገበያ ላይ ማግኘት አዳጋች ሆኖብኛል አለ፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች እንደገለጹት÷ በኮቪድ-19 ምክንያት የቆዳ ገበያው አሽቆልቁሎ የነበረ ሲሆን በአንጻሩ አሁን ላይ ገበያ መነቃቃት ሲታይበት ደግሞ የበሬ እና የበግ ቆዳ እጥረት አጋጥሟል፡፡
የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማኅበር የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ታጠቅ ይርጋ የቆዳና ሌጦ ገበያ ኮቪድ-19 በመከሰቱ የኢትዮጵያ የቆዳ ኢንዱስትሪ በጣም ተዳክሞ እንደነበር አስታውሰው÷ አሁን ላይ ግን ይህ ጉዳይ የተቀየረበት ሁኔታ እንዳለ አመላክተዋል፡፡
ሆኖም ግን ዘርፉ÷ በኮንትሮባንድ ንግድ እና በግብዓት እጥረት በተለይም የውጭ ምንዛሪ በወቅቱ አለማግኘት ከፍተኛ ችግር መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የቆዳ እና ቆዳ ውጤቶች ምርምር እና ልማት ማዕከል ተወካይ ሥራ አስኪያጅ አቶ መሀመድ ሁሴን በበኩላቸው÷ የቆዳ ምርት አሁን ላይ የተሻለ እደሆነ እና በኮቪድ ምክንያት የተቀዘቀዘው ገበያ በጥሩ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
በቀጣይም ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ ለሚልኩ የቆዳ ፋብሪካዎች የውጭ ምንዛሪ በቅድሚያ እንዲያገኙ ከብሔራዊ ባንክ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሠሩ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡
በሲሳይ ጌትነት
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.