Fana: At a Speed of Life!

የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ለመፍታት ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል የምክክር መድረክ በይርጋለም ኢንዱስትሪ ፓርክ ተካሂዷል፡፡

የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቢዝነስ ልማት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጴጥሮስ ማርቆስ እንደገለጹት ÷ ምክክሩ በዘርፉ እያጋጠሙ ያሉ የሰው ኃይልና የፋይናንስ አቅርቦት እንዲሁም የመሠረተ ልማት ችግሮችን ለመፍታት ያለመ ነው፡፡

በመድረኩ ላይ በፓርኩ ኢንቨስት እያደረጉ ያሉ ተቋማትን ጨምሮ፣ ባንኮች፣ የልማት ድርጅቶች እና አጋር አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በመድረኩ ላይም በዘርፉ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች ላይ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራስፈፃሚ አቶ መምህሩ ሞኬ÷ ባለድርሻ አካላት ዘርፉን በአግባቡ በመደገፍ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ የሚደረገውን ጉዞ መደገፍ እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ መንግሥት ግብዓቶች በአግባቡ ወደ ፓርኩ እንዳይደርሱ የሚያደርጉ ሕገ ወጥ ደላሎችን ስርዓት እንደሚያስይዝ ጠቁመው÷ የአካባቢው ማህበረሰብም ኢንዱስትሪ ፓርኩ የተቋቋመው ለራሱ መሆኑን ተገንዝቦ ጥራት ያለው ምርት ወደ ፓርኩ ማምጣት አለበት ብለዋል፡፡

የአካባቢውን ፀጥታ ለመጠበቅ እና የፓርኩን ሥራ የሚያስተጓጉል ማንኛውንም ሁኔታ ለማስተካከል መንግስት ቁርጠኛ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡

በጥላሁን ይልማ እና በታመነ አረጋ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.