Fana: At a Speed of Life!

ባንኩ የወርቅ አምራቾችን ለማበረታታት ከዓለም አቀፍ የወርቅ ገበያ ላይ የ35 በመቶ ጭማሪ አድርጎ ለመግዛት መወሰኑን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወርቅ አምራቾችን ለማበረታታት ከዓለም አቀፍ የወርቅ ገበያ ላይ የ35 በመቶ ጭማሪ አድርጎ ለመግዛት መወሰኑን አስታወቀ።

የባንኩ የከረንሲ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ አበበ ሰንበቴ በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወርቅ አምራቾችን ለማበረታታትና የኮንትሮባንድ ንግዱን ለመቆጣጠር ከመጋቢት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ከዓለም አቀፍ የወርቅ ገበያ ላይ እንደ ወርቁ ብዛት ከአስር በመቶ እስከ 29 በመቶ ጭማሪ በማድረግ ይገዛ እንደነበር አስታውሰዋል።

በዚህም ከመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ በነበሩት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ የሆነ የወርቅ አቅርቦት መገኘቱን ተናግረዋል።

በእነዚህ ዓመታት ባንኩ ከወርቅ ግብይት 1 ነጥብ 2 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አግኝቷል ብለዋል።

ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚመጣው የወርቅ መጠን እየቀነሰ በመምጣቱ አምራቾችን ለማበረታታት ለሁሉም ወርቅ አቅራቢዎች እኩል በ35 በመቶ ጭማሪ ግዥ ይፈጸማል ሲሉ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.