Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና ህንድ ግንኙነት በብዙ ነገር የተሳሰረ ዘመን ተሻጋሪ ነው – የህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና ህንድ ግንኙነት በብዙ ነገር የተሳሰረ ዘመን ተሻጋሪ ነው ሲሉ የህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማኒያም ጃይሸንከር ተናገሩ።

በኢትዮጵያ የህንድ ኤምባሲ በአዲስ አበባ ያስገነባውን የኤምባሲ ህንጻ አስመርቋል።

ህንጻውን የህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማኒያም ጃይሸንከር፣ የኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ ጋር በመሆን መርቀውታል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር በንግድ፣ ኢንቨስትመን፣ በባህል፣ በትምህርትና በሌሎች መስኮች በትብብር እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል።

ህንድ በአሁኑ ሰዓት ከአፍሪካ ሀገራት ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር በተለየ ትኩረት እየሰራች መሆኗን ጠቅሰው፥ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ወዳጅነት የላቀ ለማድረግ የጋራ ጥቅምን መሰረት በማድረግ በትብብር እንደምትሰራም አስታውቀዋል።

የኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው÷ ዛሬ የተመረቀው የኤምባሲ ህንፃ የኢትዮጵያ መንግስት የሁለቱን ወዳጅ ሀገራት ግንኙነት በይበልጥ ለማጠናከር ያለውን ፅኑ ፍላጎት ማሳያ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት 637 የህንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች መሰማራታቸውን በማስታወስ÷በሀገራቱ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.