Fana: At a Speed of Life!

የሸገር ዳቦ ፋብሪካ  90 በመቶ መጠናቀቁ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣የካቲት 29፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሸገር ዳቦ ፋብሪካ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ወደ ምርት እንደሚገባ ተገለጸ።

የግንባታ ፕሮጀክቱ አሁን ላይ 90 በመቶ የደረሰ ሲሆን በዛሬው እለትም የመጀመሪያ የማሽን ተከላውን አከናውኗል።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማም ማሽኖቹን እና አጠቃላይ የግንባታ ሂደቱን ተመልክተዋል።

ምክትል ከንቲባው በጉብኝታቸው ወቅት እንዳሉት የግንባታ ሂደቱ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በመግለፅ ምናልባትም ፋብሪካው ከፋሲካ በፊት ሊጀምር ይችላል ብለዋል።

የዳቦ ፋብሪካው ወደ ምርት ሲገባ በገበያው ላይ የሚታየውን የዳቦ እና የዱቄት አቅርቦት ችግርን ይቀርፋል ተብሎ ታምኖበታል።

በተጨማሪ በከተማዋ መግቢያዎች ይገነባሉ የተባሉ አምስት የግብርና ምርቶች መጋዘን እና የዘይት ፋብካ ግንባታ የተጀመረ መሆኑን እና ይህ በከተማዋ የሚታየውን የተጋነነ የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት አስተዋጾው እንደሚኖረው ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል።

ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው የሆራይዝን ፕላንቴሽን ከትራንስፎርመር ጋር በተያያዘ የዘገየ ቢሆንም

ፋብሪካው የሚያስፈልገውን ሀይል ማቅረብ የሚችል ትራንስፎርመር በግዢ ሂደት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከቀናት በኋላ ይጠናቀቃል።

ለዳቦ ማከፋፈያ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችም ተገዝተዋል ነው የተባለው።

ከዚህ በተጨማሪም ለአንድ አመት የሚሆን የስንዴ ግዢ መከናወኑንም ተገልጿል።

የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ግንባታ ተጠናቆ ወደ ምርት ሲገባ በቀን 1 ሚሊየን 600 ሺህ ዳቦዎችን ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል።

በሀይማኖት እያሱ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.