Fana: At a Speed of Life!

ባለሃብቶች ብዙ የተፈጥሮ ፀጋ ያለውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እንዲያለሙ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ የተዋቀረው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢንቨስትመንት አማራጮች የሚተዋወቁበት እና ገቢ የሚሰበሰብበት መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ተዘጋጅቷል።

መርሃ ግብሩ የክልሉን እምቅ የመልማት አቅም በማሳየት ለባለሀብቶች አማራጭ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ማመላከት አንዱ ዓላማው ነው ተብሏል።

እንዲሁም ክልሉ መሰረታዊ የሆኑ የህዝብ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ እየገጠመው ያለውን የበጀት ውሱንነት ለመፍታት ገቢ ማሰባሰብ ሌላኛው ዓላማው መሆኑ ተገልጿል።

መርሃ ግብሩን አስመልክቶ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ እና የክልሉ የገቢ አሰባሰብ ዐቢይ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ፀጋዬ ማሞ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ ክልሉ ብዙ ፀጋ ያለበት በአንፃሩ ግን ያለማ ነው ብለዋል፡፡

ባለሃብቶችም ይህንን ቢደግፉ እና በክልሉ መዋዕለ ንዋያቸውን ቢያፈሱ በአጭር ጊዜ ለኢትዮጵያ ብልፅግና ምክንያት የሚሆን በርካታ ስራዎች የሚሰሩበት ክልል እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

አሁን ጊዜዊ ችግር የሆነው የበጀት እጥረት አጋጥሞናል ያሉት አቶ ፀጋዬ፥ ከሁሉ በላይ ባለሃብቶች በገንዘብ ብቻ ሳይሆን ወደ ክልሉ በመግባት ሰፋፊ የኢንቨስትመንት ስራዎችን በመስራት የክልሉን እድገት እንዲያፋጥኑ ጠይቀዋል፡፡

በዛሬው መርሃ ግብርም የክልሉ ወዳጆች፣ የተለያዩ የልማት ድርጅቶች ፣ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች እና ባለሃብቶች በመሳተፍ የክልሉን ልማት በማፋጠን የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

በፌቨን ቢሻው

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.