Fana: At a Speed of Life!

 የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በተመድ  የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ  በጋራ  ለመስራት  ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር  እና በተባበሩት መንግስታትድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳች  ላይ ምክክር አካሂደዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ተወካይና የሪጂናል ቢሮው ዳይሬክተር አውሬሊያ ፓርቲዚያ ካላብሮ ÷ድርጅቱ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በግጭቱ ምክንያት ጉዳት በደረሰባቸው በአፋርና በአማራ ክልሎች የሚተገበር የሴቶችን የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ፐሮጀክት ቀርጾ ወደ ተግባር ለመግባት እየተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው÷ የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማትና የድጋፍ ስራዎችን እያከናወነ በመሆኑ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡

በሰሜኑ የኢትዮጵያ  ክፍል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ከገጠማቸው ስነ-ልቦናዊ ችግር ተላቀው ወደ ጤናማ ህይወት እንዲመለሱ ለማስቻል የተጀመሩትን ጥረቶች በዋናነት ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ለማጎልበት የስራ ፈጠራ ስልጠና ማመቻቸትና የገቢ ማስገኛ ዘርፎችን የማስፋት ስራን ድርጅቱ እንደሚደግፍ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም ሚኒስቴሩ ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ጋር በችግር ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ፕሮግራሞች ላይ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱን ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.