Fana: At a Speed of Life!

1ሺህ 24 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 1ሺህ 24 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ ፡፡
በዛሬው ዕለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ የመመለስ ሥራ 1ሺህ 24 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ የተቻለ ሲሆን÷ ከእነዚህ ውስጥ 23ቱ ሕጻናት መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራም÷ 40 ሺህ 911 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.