Fana: At a Speed of Life!

ሕንድና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉበት አግባብ ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕንድና ኢትዮጵያ በልማት እንዲሁም በበርካታ ዘርፎች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉበት አግባብ ላይ ተወያዩ።

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ጃይሻንካርን በጽኅፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በትምህርት፣ ጤና እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ፍሬያማ ውይይት ማካሄዳቸው ተጠቁሟል፡፡

ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ በዚህ ወቅት ህንድ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ላሳየችው መርህን የተከተለ ጽኑና ገንቢ አቋም ምስጋና ማቅረባቸውን የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ የሁለትዮሽ የትብብር መስኮች ላይ እንዲሁም በልማት ዘርፍ መሥራት በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ላይ ተወያይተዋል።

ከዚህ ባለፈም በአኅጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይም ምክክር አድርገዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.