Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የተሻለ የታክስ አሰባሰብና የበጀት አጠቃቀምን ለመፍጠር እንደሚሠራ የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ የተሻለ የታክስ አሰባሰብና የበጀት አጠቃቀምን ለመፍጠር እንደሚሠራ የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ገለጸ፡፡
የክልሉ ገንዘብ ቢሮ በመንግስት ፋይናንስ እና ታክስ አስተዳደር ዙሪያ፥ ለክልል፣ ለዞን፣ ለወረዳ እና ለከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ስልጠና እየሰጠ ነው።
የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ጥላሁን መሃሪ በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በክልሉ የተሻለ የታክስ አሰባሰብና የበጀት አጠቃቀምን ለመፍጠር ይሠራል ብለዋል፡፡
ስልጠናውን መስጠት ያስፈለገውም በክልሉ የተሻለ የሃብት አሰባሰብና አጠቃቀም ስርአትን ለማሳደግ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
የክልሉ በጀት የተለያዩ የአሠራር እርከኖችን ተከትሎ እንደሚቀርብ፣ የበጀት ድጎማ ቀመር ምንነት እና አስፈላጊነትን በተመለከተ የባለድራሻ አካላትን ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ስልጠና መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ስልጠናው በሁለት ዙሮች ለክልል፣ ወረዳ እና የከተማ አስተዳደር የፋይናንስ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡
በይስማው አደራው
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.