Fana: At a Speed of Life!

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር  ሊግ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ወላይታ ዲቻ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ28ኛው ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ዲቻ ጅማ አባ ጅፋርን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ረፋድ ላይ በተደረገው ጨዋታ ጅማ አባ ጅፋር በመሱድ መሀመድ ጎል እስከ እረፍት መምራት ቢችሉም ከረፍት መልስ አበባየሁ አጂሶ ባሰቆጠሯቸው ጎሎች ወላይታ ዲቻ ሙሉ 3 ነጥብ ማግኘት ችሏል፡፡

የጦና ንቦች ማሸነፋቸውን ተከትሎ ነጥባቸውን 41 በማድረስ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር እኩል 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል፡፡

በተመሳሳይ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዲያ ሆሳዕና ከሰዓት ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ  ውጤት ተጠናቋል፡፡

በጨዋታው አማኑኤል ገብረሚካኤል ለጊዮርጊስ የመጀመሪያዋን ግብ በማስቆጠር ቀዳሚ ቢያደርግም÷ ኤፍሬም ዘካሪያስ ከረፍት መልስ ሀዲያ ሆሳዕናን  አቻ ማድረግ ችሏል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬ ነጥብ መጣሉን ተከትሎ የዋንጫ ፉክክሩ ይበልጥ አጓጊ እየሆነ የመጣ ሲሆን÷ ነገ ፋሲል ከተማ ሰበታ ከተማን የሚያሸነፍ ከሆነ የነጥብ ልዩነቱ 1 ብቻ ይሆናል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.