Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሴቶች የሰላም ግንባታ ይፋ ማድረጊያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ሴቶች የሰላም ግንባታ ይፋ ማድረጊያ መርሐ ግብር ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በተገኙበት ተካሄደ፡፡

የሰላም ግንባታ ማብሰሪያ መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ባስተላለፉት መልዕክት ÷ በሀገራችን የተፈጠሩ ግጭቶች ንጹሀንን ህይወታቸውን አንዲያጡ ከማድረጉም በተጨማሪ ሴቶችንና ህጻናትን ለከፍተኛ ጉዳት ዳርጓል ብለዋል፡፡

በሰላም እጦት የተነሳ በርካታ ንጹሀንን አጥተናል፤ እንዲሁም በቅርቡ በንጹሀን ላይ የተፈጸመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ የጭካኔና የአረመኔ ጥግንም አሳይቶናል ነው ያሉት፡፡

በዚህም ዋነኛ ሰለባ የሆኑት ሴት የህብረተሰብ ክፍሎች እንደመሆናቸው መጠን ለሰላምና ግጭት አፈታት ላይ ወሳኝ ሚና ማኖር ይገባል ማለታቸውን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.